معرض صور

ታላቁ ጌታችንን አላህን መውደድና እርሱን ማፍቀር

أعظم محبوب ـ باللغة الأمهرية | ታላቁ ተወዳጅ - አማርኛ

 

بسم الله الرحمن الرحيم

الحمد لله رب العالمين و صلى الله وسلم  على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين             

أعظم محبوب

 

ታላቁ ጌታችንን አላህን መውደድና እርሱን ማፍቀር

 

እያንዳንዷ ነፍስ በጎ  የዋለላትን አካል  በጣም ትወዳለች   ለምሳሌ ልጅ ወላጅ አባቱን በጎ ስለሚውልለት በእጅጉ ይወደዋል  በሽተኛ ሰው ፈውስ ያገኝ ዘንድ ምክንያት የሆነለትን ሰውና የተባበረውን  በጣም  ይወዳል ዓሊም ሰው አስተማሪውን ይወዳል  ግፍና በደል የደረሰበት ሰው ረዳቱንና ከጎኑ  የሚቆምለትን ይወዳል የሰው ልጆች  በሙሉ ስሜታቸውና ባሕሪያቸው ይህን ይመስላል

ታዲያ ለሰው ዘር በሙሉ እጅግ በጣም ታላላቅ የሆኑ ዉለታዎችን የዋለ የሆነውን ጌታችንን አላህን መውደድ በተመለከተ ሁኔታው እንዴት ነው?

እርሱ አላህ ወንጀልን መሃሪ የሆነ ጌታ ነው  የልብ ጭንቀትን፣ ትካዜን፣ብቸኝነትንና ሓሳብን  አርቆ ደስተኛ የሚያደርግ ጌታ ነው  ስሜቱ የተጎዳና ሞራሉ የተሰበረ የላሸቀን  ሰው  ተደፍቶ የቆየውን አንገቱን ቀና እንዲያደርግ የሚያስችል  አዛኝ ጌታ ነው   አላህ ድሃን ሃብታም ያደረገ  ያላወቀን እንዲያውቅ የሚያደርግ ፣  የተሳሳተን ትክክለኛውን  መንገድ የሚያመላክት ጌታ ነው  አላህ ፅኑ አቋም የሌለውን  ይመራል  እርዳታ ያስፈለገውን አካል ይረዳል የታሰረን ግለሰብ ከእስር እንዲለቀቅና እንዲፈታ ያደርጋል አላህ  የተራበን ያበላል  የታረዘን ደግሞ ያለብሳል  የተጠማን ያጠጣል በሽተኛ አካልን በደምብ አድርጎ  ይፈውሳል  ተውባ ያደረገን ሰው ተውባውን(ፀፀቱን) ይቀበላል መልካም ስራ ለሚሰራ ታላቅ ዋጋ ይከፍላል ተበዳይን ይረዳል  ጥጋበኛን አይቀጡ ቅጣት የሚቀጣ   አረመኔን የሚያዋርድ ነውርን የሚሸፍን የሚሰውር   ልብ ውስጥ ዘላቂ ሰላምን የሚፈጥር የሆነ ሀያልና ቸር ጌታ ነው

ለዚህም ነው የአላህ ውዴታ ቅን ለሆነ ልብ  ህይወትና እርካታን የሚያገኝበት ነጥብ የሆነው ለሩህ ቀለብ  ለልብ ደስታ ነው ምክንያቱም አላህን የማትወድ ሩህ እርካታ፣ ደስታና ስኬት  ፈፅሞ አታገኝም  ንፁህ ቀልብ  የአላህን ውዴታ ካላገኘ የሚደርስበት በሽታ የሰው ዓይን ብርሃን ከመጥፋትና   መስማትን ከተሳነው የሰው ጆሮ   እጅግ በጣም  የበረታ ይሆናል

እጅግ በጣም ደካማ በሆነ ሁኔታ ላይ እያለህ በሶስት ጨለማዎች ውስጥ ስትሆን   ከእናትህ  ማህፀን ውስጥ ካለህበት ወቅት  ጀምሮ አላህ የዋለልህን ውለታ አስታውስ   በቀጣይ ሁኔታ ልዩ ክትትል በማድረግ ይጠብቅህ የነበረውን ጌታህን አላህን  አስታውስ  ከማህፀን ውስጥ እያለህ ይመግብህ የነበረ ጌታ መሆኑንም አትዘንጋ በመቀጠልም   አላህ  ስለምንም ነገር የማታውቅ ጥሬ መሃይም  ስትሆን ወደዚህ ዓለም እንድትመጣ አደረገህ  ከዚያም  አዛኝ የሆነችን እናት አላህ አዘጋጀልህ መደበልህ  ከህይወቷ ይበልጥ ለአንተ ጠንካራና አስተማማኝ ድጋፍ  ትኩረት እንክብካቤ የምትሰጥህ አደረጋት   ጡትዋን በደንብ እንዳስፈላጊነቱ  እንድታጠባህ አደረጋት   እንዲሁም ከአንተ በእጇ ያዝ በማድረግ አንተን ለማፅዳት ስትል  ቆሻሻህን ታጥብልህና ታስወግድልህ ዘንድ     በጥቅሉ የምትችለው የሆነን መልካም ነገር በሙሉ ተጠቃሚ ትሆን ዘንድ ወደ አንተ እንዲደርስ ለማድረግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል  ሌት ቀን ደፋ ቀና  የምትል እናት ያዘጋጀልህ አላህ መሆኑን አትርሳ   

የሰው ልጅ ቆም ብለህ አስብ ውለታ የዋለልህን አካል በአመፅ መጋፈጥ ያሳፍራል ፍላጎቱንም   መቃረን አትፈልግም  ታዲያ ብዙ ፀጋዎችን የዋለልህን ጌታ አላህን እንዴት ትቃረናለህ?

 ከቀደምት ሰዎች መካከል አንዱ እንዲህ ብሏል  ፡-(አላህ የዋለልህን ውለታ መረዳት ከፈለክ  ይቺን ዓይንህን ለተወሰኑ  ደቂቃዎች ጭፍን አድርጋት)

አላህ እንድህ ብሏል፡-(ማንኛውም በናንተ ላይ ያሉ ፀጋዎች ሁሉ ከአላህ የተገኙ ናቸው አንዳች ጉዳት ባገኛችሁም ጊዜ ወደርሱ ትጮኻላችሁ ) ምእራፍ አን-ነሕል. 53

አላህ እንዲህ ብሏል፡-(አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ከሰማይም ውሃን ያወረድና በርሷም ለናንተ ሲሳይ ይሆናችሁ ዘንድ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ያበቀለ ጌታ ነው መርከብንም ባሕሩ ላይ መጓዝ  ትችል ዘንድ በትዕዛዝ ገራላችሁ  ወንዞችንም ገራላችሁ ፀሐይንና ጨረቃንም  ዘወትር ተጓዦች አድርጎ ገራላችሁ ሌትንና ቀንንም ገራላችሁ ለሕይወት የሚያስፈልጋችሁንም ነገርች ሁሉ ሰጥቷችኋል  የአላህን ፀጋዎች  ቆጥራችሁ አትዘልቋቸውም  የሰው ልጅ በእርግጥ በዳይ ከሓድ ነው ) ፍእራፍ ኢብራሂም. 34

አላህ ከዋለልህ ፀጋዎች መካከል ያለአግባብ ስምህንና ክብርህን  ዝሙት ሰርቷል ብሎ ያረከሰና የተቸህን ሰው እንዲገረፍ በማድረግ ክብርህ እንዲጠበቅ ያዘዘ  ንብረትህን የሰረቀ ሰው እጁ እንድቆረጥ በማድረግ ንብረትህ እንድከበር ያደረገ  ጉዞ ላይ በምትሆን ወቅት እንዳትቸገር ሲል ሶላትን በተመለከተ ያቃለለልህ  በቅዝቃዜና ብርዳማ ወቅት ላይም  ሆነ በሌላ ወቅት በመልበስና በማውጣት እንዳትቸገር ሲል  በኹፍና ካልሲ ላይ ማበስን በተመለከተ  ልክ እግርን በውሃ እንደማጠብ የቆጠረልህ   ሕይወትህ ሳትበላሽ  ለማቆየት አካላዊ ጤንነትህን ለመጠበቅ ሲል  በክት መመገብን በመፍቀድ እንክብካቤ ያደረገልህ   ጉዳት የሚያደርስን ነገር በተመለከተ ለመከላከል ለመራቅ ለመቆጠብ ሲባል  ፈጣን ወይም  ዘግይቶ የሚመጣ ቅጣት በመደንገግና በመዛት እንድትርቅ ያደረገ አዛኝ ጌታ ነው

የአላህ እዝነት በዓለም ላሉ ፍጥረታት ሁሉ ያዳረሰ መሆኑን

አላህ እንዴት እንደሚያዝንልህ እንደሚጠብቅህ እንደሚንከባከብህ ረጋ ብለህ አስተውል አስብ  እንደሚታወቀው የሰው ልጅ ራሱን ከመጠበቅ የተሳነው እጅግ ደካማ ነው ያለ አላህ  ሀይልም ጉልበትም  ችሎታም መላ ብልሀትም ብቃቱም  የለውም

የሰው ልጅ በአላህ ውሳኔ የሚንቀሳቀስ ከመሆኑ አንፃር መርጦ የመስራት እድሉን ቢሰጠውም  በበረሃ ሜዳ ላይ እንደተጣለ  በቀኝና በግራ አቅጣጫ ንፋስ እንደሚያገላብጠው እንደ ወፍ ላባ መሆኑን  መተመለከተ የራሱ ልብና ማንነቱ  ይመሰክራል  የሰው ልጅ ህይወት  በባሕር ላይ እንደምትጓዝ ንፋስ እንደፈለገ የሚያንቀሳቅሳትና  ከባድ ማዕበልም ከፍ ዝቅ እያደረገ እንደሚጫዎትባት ጀልባ መሆኗን ያረጋግጣል   የሰው ልጅ የአላህ ውሳኔ በርሱ ላይ ተፈጻሚ ይሆንበታል  የሰው ልጅ ለራሱ ጉዳትን ጥቅምን ሞትን ሕይወትን ከሞት በኋላ መቀስቀስን መቆጣጠር የማይችል ደካማ  አቅም የሌለው  ዋጋ ቢስ ፍጡር ነው 

አላህ ለኛ ትልቅ ውሌታን  ይውልልናል   የሰው ልጅ ግን አላህ ያዘነለት ሲቀር ውሌታውን በመካድ ያስተናግደዋል

ታላቅ  ከሆነው ውሌታው  ጋር  ካንተ የተብቃቃ ሆኖ እያለ ውዴታውን ይገልፅልሀል   አንተ ወደርሱ ከጃይ ከመሆንህ ጋር  ወደኋላ ስታፈገፍግ እርሱ ግን አንተ ወደርሱ እንዲትቀርብ ያነሳስሀል    

በሰማያትም በምድርም ያለው ሁሉ የርሱ ነው አንድት ቅንጣት ታበድረው ዘንድ ጠየቀህ ንፉግ ስስታም ስለሆንክ እምቢ አልክ  አላህ የሰው ልጅ ይጠይቀውና ይለምነው  ዘንድ አዘዘ የሰው ልጅ ግን እምቢ አለ   አላህ ግን ለባሪያው ሳይለምነው ታላላቅ ስጦታዎችን ለገሰው  የሰው ልጅ ይበልጥ የሚያዝንለትን ጌታውን ትቶ ለማያዝንለት አካል ብሶቱንና  ጭንቀቱን ያወያየዋል የማይበድለውን አላህን በደለኝ እያለ ያማርራል  የሰው ለጅ ሆይ አላህ ጤና አፊያ ገንዘብ ክብር ሲሰጥህ በዚህ አላህ በሰጠህ ፀጋ አላህን ታምፅበታለህ  አላህ በሩን ክፍት አደረገልህ አንተ ግን መቆርቀርም ሆነ መግባት አልቻልክም

ወደተከበረችው ጀነት የሚጠራህ መልእክተኛ ላከልህ አንተ ግን መልእክተኛውን አመፅክ  በዓይኔ ያየሁትን ነገር በጆሮየ ለሰማሁት ብዬ ፈፅሞ አልተወውም አልክ   ነገር ግን ይህ ሁሉ ሲከሰት አላህ አንተን ከእዝነቱ ተስፋ እንዲትቆርጥ አላደረገህም  ይልቁንም በማንኛውም ጊዜ እኔን ስታስታውሰኝ  እኔም አስታውስሀለሁ  ፣ሌትም ይሁን ቀን ወደኔ ከተመለስክ  ተውባህን እቀበልሀለሁ ወደኔ ስንዝር ብትቀርብ እኔ  ደግሞ ወደ አንተ  አንድ ክንድ (ባእ) እቀርባለሁ  አንተ ወደኔ በርጋታ  ብትጓዝ እኔ ደግሞ  ወደ አንተ እፈጥናለሁ የሰው ልጅ ሆይ ምድርን የሚሞላ ወንጀል ተሸክመህ ከኔ ዘንድ ብትመጣ በኔ ላይ ሌላ ኋይልን እስካላጋራህ ድረስ ምድርን የሚሞላ ምህረት ይዤ እጠብቅሐለሁ  ወንጀልህ ሰማይ ላይ ቢደርስ  ከዚያም ይቅር እንድልህ ከጠየከኝ ይቅር እልሀለሁ

ከአንዱ ብቸኛ ከሆነው  ጌታችን አላህ  በቀር  ቸር ማንም የለም አላህ  እኔ ባሮቼን ከመተኛ ጎኖቻቸው ከማረፊያ ፍራሾቻቸው ላይ እያሉ ከመጥፎ ነገር የምጠብቃቸው እኔ ብቻ ነኝ ይላል  የሰው ልጆች ግን   እኔን በማመስገናቸው ፋንታ ታላላቅ ወንጀል በመፈፀም ከእኔ ጋር በግልፅ በይፋ ጦርነት  አውጀዋል  ጌታችን አላህ  አጋንንቶችና የሰው ልጆች በጣም አስገራሚና አሰደናቂ  በሆነ ሁኔታ እና ታሪክ  ላይ ይገኛሉ ይላል ፈጣሪያቸውና መጋቢያቸው  እኔ ብቻ ስሆን  ከእኔ  ውጭ ሌላን አካል  ያመልካሉ   እኔ ሲሳይን እለግስላቸዋለሁ  በብዛት የሚያወሱትና የሚያወድሱት ከእኔ  ሌላ የሆነን  አካል ነው ከእኔ ወደ ምድር  ለባሮቼ  መልካም በጎ ነገር ሁሉ ይወርዳል  ነገር ግን መጥፎ ተግባራቸው (ሀፅያታቸው)  ወደኔ ያርጋል ይወጣል  እኔ ከእነሱ በእጅጉ  በራሴ የተብቃቃሁ ስሆን የተለያዩ  ፀጋዎችን በመለገስ ለነርሱ ያለኝን ውዴታ እገልፅላቸዋለሁ  ፍጡራን በእጅጉ ሁል ጊዜ  ወደኔ ከጃዮች ሆነው እያሉ እኔን በመቃረን ይገኛሉ  አንድን ነገር ለእኔ ሲል የተወ ከሚፈልገው በላይ እጥፍ ድርብ አድርጌ እሰጠዋለሁ

እኔን ሁል ጊዜ  ለሚያስታውሱኝ ባሮቼ ለየት ላቅ  ያለ ደረጃ አዘጋጅቼላቸዋለሁ    አመስጋኞችን  እወዳቸዋለሁ አክልላቸዋለሁ   እኔን የሚታዘዙትን በእጅጉ አከብራቸዋለሁ  መልእክቱ በትክክል ደርሷቸው አንቀበልም የሚሉ አመፀኞችንም ከእዝነቴ ተስፋ ቆራጮች እንዲሆኑ አላደርጋቸውም   ተውባ በማድረግ ወደኔ ከተመለሱ  ተውባቸውን እቀበላለሁ  እኔ ተመላሾችንና  ከመጥፎ  ተግባር የሚፅዳዱ ባሮቼን  እወዳለሁ

     እኛ ወንጀል እንሰራለን እርሱ  አላህ ግን ተውባ እናደርግ ዘንድ ይጠራናል ይመክረናል

የሰው ልጅ ሆይ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ታላቅ  እዝነት ልታውቅ ልትረዳ  ይገባሀል ወንጀል ሲሰሩ ወደርሱ ይመለሱና ተውባ ያደርጉ ዘንድ እንደት እንደሚጠራቸው እስኪ  እረጋ ብለህ አስተውል

ወዳጆቹንና ባሮቹን ያሰቃዩ የሆኑ ሰዎችን በተመለከተ እንዲህ ሲል በቀጣዩ አንቀፅ ተናግሯል፡- (እነዚያ የሴትና የወንድ አማኞችን የፈተኑ እና ያልተፀፀቱ ወገኖች የጀሐነም ቅጣት ተዘጋጅቶላቸዋል አቃጣይ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ) ምእራፍ አልቡሩጅ .10

 ሀሰን አልበስሪ  አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ሲሁ ተደምጠዋል ፡-( እስኪ ይህን  አስገራሚ ቸርነት ተመልከቱ  የአላህን ወዳጆች ጨፍጭፈው ገደሉ  ነገር ግን አላህ ተውባ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ አደረገላቸው)

አላህን ከሚገዙ ሰዎች መካከል አንዱ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡- አንድ መንገድ ላይ የተከፈተ በር አየሁ ከዚህ በርም  ህፃን ልጅ እያለቀሰና እርዳታ እየጠየቀ ወደ ውጭ ወጣ ወላጅ እናቱ ደግሞ ከኃላው ተከትላ ታባርረዋለች ከዚያም በሩን ከፊቱ ላይ ዘጋችበትና ከቤት ውስጥ ገባች ህፃኑም እርቆ ሳይሄድ ቆም ብሎ ማሰብ ጀመረ ከዚያ ከወጣበት ቤት ውጭ ሌላ መሸሻና መጠጊያ ማግኘት አልቻለም ከወላጅ እናቱም ሌላ የሚያስጠጋው አካል አላገኘምና በጣም እዝነት የተሰማው ሲሆን ትቶት ወደሄደው  ቤት ተመለሰ ከዚያም ብርቱ በሆነ መልኩ በሩ ተዘግቶ አገኘው ህፃኑም በሩን ትራስ በማድረግ ጉንጩን ከበሩ ላይ በማስደገፍ ተኛ  በመቀጠልም እናቱ ወደ ውጭ ወጣች  ልጁ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ እናቱ ተመለከተች አካሏን ከልጇ ላይ ከመወርወር ውጭ እራሷን መቆጣጠር አልቻለችም  ከዚያም ልጇን እቅፍ አድርጋ በመሳምና በማልቀስ ልጄ ሆይ ከእኔ ሸሽተህ ወደየት ነው የምትሄደው ከእኔ ሌላ የሚያስጠጋህ አካል ማን አለ ብለህ ነው ልጄ ሆይ  አትቃረነኝ እኔን ባለመታዘዝህ ሳቢያ ተፈጥሮየ ከሆነው ባህሪ ውጭ ወደሆነ ባህሪ አትገፋፋኝ በማለት አልመከርኩህምን በማለት እቅፍ አድርጋ በመያዝ ወደቤት አስገባችው

  አንተ የሰው ልጅ ሆይ እስኪ ረጋ ብለህ እዚህ ላይ እኔን ባለመታዘዝህ ሳቢያ ተፈጥሮየ ከሆነው ባህሪ ውጭ ወደሆነ ባህሪ አትገፋፋኝ የሚለውን የዚህችን እናት ለልጇ ያስተላለፈችውን ምክር በጥሞና አስተውል

 በቀጣዩም በተረጋጋ ሁኔታ የመልእክተኛውን ንግግር አስተውል ፡-(አላህ ለባሪያዎቹ እናት ለልጇ ከምታዝንለት ይበልጥ ያዝናል )

ለሁሉም ነገር የሰፋ ከሆነው ከአላህ  እዝነት ጋር ሲመዛዘንና ሲነፃፀር   እናት ለልጇማዘኗ ምንም ደረጃና ቦታ የለውም  ግምትም አይሰጠውም

እኛ ፍጡራኖች ከአላህ ውጭ ለአይን ቅፅበት እንኳ ያክል እራሳችንን የምንችልበት አቅሙ የለንም

ለዚህም ነው  ትክክለኛ ሙስሊም ምንጊዜም ጌታውን አላህን እንዳስደሰተ የሚኖረው  በአድንቆት እየተገረመ መላ ሕይወቴ  በዚህች ዓለም ውስጥ የመኖር ዋስትናዋ  እንዲጠበቅ እርሱን በማስደሰት ላይ ሆኖ እያለ  ጌታየን እንዴት  አስቆጣዋለሁ የሚለው  እድለኛና ስኬታማ  መሆኔ እርሱን ከመውደድ ከማስታወስ ወደ አላህ  ከመቀራረብ ጋር የተሳሰረ ሆኖ እያለ   ከአላህ እንዴት ፊቴን በማዞር  አፈነግጣለሁ

ሁኔታው አባቱ እንደሚመግበው እንደሚያጠጣው እንደሚያለብሰው  በጥቅሉ በጥሩ ሁኔታ እንደሚንከባከበው የሚያስፈልገውን ሁሉ በሚያሟላለት ልጅ ይመሰላል   ይህ ልጅ ከእለታት አንድ ቀን አባቱ ለሆነ ጉዳይ ላከው መንገድ ላይ ጠላት አገኘው አሰረው ከባድ በሆነ መልኩ ቀፈደደው በመቀጠልም ወደ ቀንደኛ ጠላቶች ሀገር ይዞት ሄደ ከባድና ዘግናኝ የሆነን ቅጣት ቀጣው  ይህ ልጅ በዚህ ስቃይ ላይ እያለ  አባቱ ይውልለት የነበረውን መልካም ውሌታ ማስታወስ ጀመረ ልጁን  አሁን ያለበት ሁኔታ በጣም አበሳጨው  ከወላጅ አባቱ ጋር በነበረ ጊዜ የነበረበትን  የድሎት ሕይወት ማገናዘብ ጀመረ  በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ በመጨረሻም ይህ ጠላት  እንደ እንስሳ አስተኝቶ ሊያርደው በተዘጋጀበት ወቅት ይህ ልጅ ድንገት ወደ ተወለደበት ሀገር አቅጣጫ ዞረ  በመቀጠልም ወላጅ አባቱ ለርሱ በጣም የቀረበ ሆኖ አየው  ይህ ልጅ  በፍጥነት ከወላጁ ፊት ለፊት የወደቀ ሲሆን እርዳታ እየጠየቀ አባቴ አባቴ አባቴ እያለ መጣራት ጀመረ  ልጅህን ተመልከት ያለበትንም ሁኔታ አስተውል እያለ ባቄላ የሚያክል እምባው በጉንጩ ላይ እየወረደ  አባቱን እቅፍ በማድረግ አጥብቆ ያዘው  ይህ ልጅ  ጠፍቶ ስለነበር በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ጠላቱ ፈጥኖ በመድረስ ድንገት  ከአጠገቡ ቆም አለ

 ይህን ክስተት እስኪ ረጋ ብለህ  አስብ  ይህ አባት ለዚህ ጠላት የልጁን ሕይወት አሳልፎ ይሰጣል ተብሎ መቼም አይታሰብም

 ወላጆች ለልጆቻቸው ይህን ያክል የሚያዝኑ ከሆነ  ጌታችን አላህ ደግሞ ለባሮቹ ከወላጆች ይበልጥ እጅግ አዛኝ መሃሪ መሆኑ  አያጠራጥርም   

እጅግ በጣም የሚገርም ሁኔታ

እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር አላህን አውቀኸው አለመውደድህ ፣ጥሪውን ሰምተህ ለመታዘዝ መዘግየትህ ፣ከርሱ ጋር መነገድ ያለውን ትርፍ እያወቅክ ሌላን መምረጥህ ፣የቁጣውን አደገኛነት እያወቅክ የሚያስቆጣውን ተግባር መፈጸምህ፣ እርሱን ማመፅ የሚያስከትለውን የመንፈስ ጭንቀት እያወቅክ እርሱን በማምለክ እርካታንና መረጋጋትን አለመፈለግህ

ከአላህ መንገድ ውጭ መሆን ልብህን ምን ያህል በጭንቀት እንደሚጨምቀው እያወቅክ እርሱን በማስታወስና በመገዛት የልብህን  ደስታና እርካታ መመለስ አለመቻልህ

ከእርሱ ውጭ በሆነ ፍጡር ላይ ልብህ ሲንጠለጠል የሚያስከትለውን ስቃይ እያወቅክ ከእርሱ ውጭ ከሆነ አካል ሁሉ ሸሽተህ ወደ እርሱ ሙሉ ለሙሉ አለመመለስህ ነው ከዚህም በላይ የሚያስገርመው ያለ እርሱ እንደማይሆንልህና ለሁሉም ጉዳይህ የእርሱ እርዳታ የግድ መሆኑን እያወቅክ ከእርሱ መራቅህና ከእርሱ የሚያርቅህን በፅኑ መፈለግህ ነው

በአላህ መልእክተኛr እና  በቤተሰቦቻቸው ላይ  የአላህ ሶላትና ሰላም ይውረድ

ጌታችን ሆይ! ጭንቀታችን የመጨረሻ ግባችን ዱንያን አታድርግብን

እርምጃችንም ወደ እሳት አታድርግብን መርጊያችን /መኖርያችን  ጀነት አድርግልን   አሚን

                                                           

مطوية تحبيب الناس في خالقهم

من نحن

نسعى إلى غرس تعظيم الله في النفوس، من خلال نشر منتجات متميزة، مقروءة ومسموعة ومرئية، ومن خلال فعاليات دعوية متنوعة.

الأرشيف

جميع الحقوق محفوظه مشروع تعظيم الله © 2020
تطوير وتصميم مسار كلاود
تطوع الأن